አንዳንድ ጋዜጠኞች “አማረ አረጋዊ አሁንም ከወያኔ ስርአት ጋር ይሰራል” ሲሉ ይፅፋሉ። ሌሎች ደግሞ፣ ‘በቂ ገንዘብና ጠንካራ መንፈስ ስላለው ተቋቁሞአቸው እንጂ፣ እንደማንኛውም የግል ጋዜጣ ተፅእኖ እየተደረገበት ነው። መንግስት ከሰጠው የመኖሪያ ኪራይ ቤት አስወጥተውታል። የግል ቤት ተከራይቶ እንዳይኖርም በተለያየ ዘዴ ያሳድዱታል። ከዚያም አልፈው የሚስቱ ወላጆች ላይ ጭምር ችግር ፈጥረውበታል’ ሲሉ በተለየ ያዩታል። በዚህም ተባለ በዚያ አማረ ዝምተኛ አይደለም። አከራካሪ እንደሆነ ቆጥሎአል። ይህ ብርቱ ጎኑ ነው። ይለናል ተስፋዬ ገ/አብ በቅዳሜ ማስታወሻ ብሎጉ:: ሙሉውን ጽሁፍ ይህችን ጠቅ በማድረግ ያንብቡት::
በፍቃዱ ዘ ሃይሉ ደግሞ በርካታ ጋዜጦች ታገዱ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ታገደ፣ በመንግስት ያልተወደዱ ዘፈኖች በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ ሬዲዮ ጣቢያዎች እንዳይተላለፉ ታገዱ፣ አንዳንድ መጽሃፍቶች ሜጋ መጽሃፍት ማከፋፈያ ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ፣ የተቃዋሚ ድረገጾችና ጦማሮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ ታገዱ፣ የጀርመንና የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮዎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰሙ ታገዱ፣ …. ታገዱ፣ ታገዱ፡፡ ይላል ዘ ዲክታተርን ኢድና ሞል እንዳይታይ መታገዱን በማስመልከት የጻፍው ብሎግ::
ዞን ናይን የተሰኝ በአስር ጀማሪ ጦማሪያን የተጀመረ አዲስ ብሎግ በዚህ ሳምንት በርካታ ጽሁፎች አስነብቦናል:: ሁሉንም ጽሁፎች ወድጃቸዋለሁ መምርጥ ስላለብኝ ግን ሁለቱን ጀባ ልበል:: ዘላለም ማልኮም የሁለት ‘ሚኒስትሮች’ ወግ እና “የቃሊቲው መንግስት” እኔ እንዳነበብኩት በሚል ርእስ የጻፉትን:: በመጀመሪያ ከዘላለም ጽሁፍ አንድ አንቀጽ እንካችሁ:
የነTwtter ሚና ከፍተኛ እንደነበር የታየበት የአረቡ አለም ፀደይ (The Arab Spring) ፍሬ ካፈራና ሁሉም በየጓዳው መደንገጥ በያዘበት ሰሞን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቅ ብለው ጥቅም ላይ ስላልዋለው 3 ሚሊየን ሄክታር መሬታችን፣ ስለ ህዳሴው ግድብ ተስፋና መከራ፣ ስለ የተለያዩ እርዳታዎች፣ ስለውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የግንቦት 20 እንኳን አደረሳችሁ መልእክት ወዘተ tweet ያደርጉና ‘የሆሊውድ’ መንፈሳቸው እንደገና ሲቆሰቆስ፡
“I wanted to upload photos of this moments but the twitter app on this iphone is not letting me do it, maybe its [it’s] the network” እንዲሁም “here are some photos I promised…” ብለው ጥያቄ ያጭሩብናል፣ ይሄ ነገር እንዴት ነው? ያስብሉናል፡፡
– የApple ምርት የሆነውን iphone መጠቀማቸው ጠዋት ማታ ከሚከሱት ኒዮ ሊበራሊዝም አቀንቃኞች ጋር የጓዳ ግንኙነት አላቸው እንዴ? ሲያስብለን፣
– “…maybe its [It’s] the network” ሲሉ ደግሞ ‹‹ለካ ቴሌ ቤተሰቦቹንም አሰመርሯል እያልን ብለው ብለው “Ethio Telecom SUCKS” እንዳይሉ እንፈራለን፡፡››ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ::
አቤል ደግሞ ሰሞኑን በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የተጻፈውን መጻሀፍ እኔ እንዳነበብኩት በሚል ርእስ አስቃኝቶናል:: አንድ አንቀጽ እንካችሁ
የመጽሐፉ ይዘት መንግስት እሰረኞቹን መያዝ ከተጀመረበት ከጥቅምት 22 1998 ዓ.ም. ጀምሮ የመሰረተ ዐሳቡ ክቡድነት ያህል ለሀገሪቱ መጻዒ ጊዜ አንዳች ነገር ባላበረከተ ይቅርታ ከእስር እስከተፈቱበት ሐምሌ 13 1999 ዓ.ም. ድረስ ጥቃቅን ነገሮች ሳይቀር እየዘረዘረ ያስቃኘናል፡፡ጥቅምት 22 ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አከባቢ ይጀምርና ራሱ በተባራሪ የሚያገኛቸውን መረጃዎች ሲጠቃቅስ ይቆይና በቁጥጥር ስር ሲውል ደግሞ ወደ ወህኒ ቤት ይዞን ወርዶ በትዝታዎቹ ተመስጦ ውስጥ ይከተናል፡፡ በተደደጋጋሚ በመታሰሩ፣ ብዙ ጊዜ ቃሉን ስለሰጠና በሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች በሸገር ያሉ ወህኒ ቤቶችን ከነመንገዶቻቸውን ፣ ከነመርማሪዎቻቸው እና ዘቦቻቸው ጥንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ከቃሊቲ በተጨማሪ እንደ ዓለም በቃኝ እና ማዕከላዊ ያሉ ዝነኛ እስር ቤቶችን በነዋሪነት ስለሚያውቃቸው እያንዳንዷን ኮሽታ በጥንቃቄ እንዲያስተውል ረድተውታል፡፡ስለወንጀል ምርመራ ቆይታው ካሰፈረውና ፈገግ ያሰኘኝን ተረክ ላቀብላችኹ፡፡ ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ::
አቤ ቶኪቻው ኑ… ፌስ ቡክ ሰፈር እንሰባሰብ! ይላችኋል:: ለምን ብትሉ አንድ አንቀጽ እንካችሁ:
እውነቴን ነው የምልዎ እንደኔ ጨዋታ ወዳድ እና ወሬ ለምን ያምልጠኝ ያሉ ከሆኑ፤ ወይም በዘመናዊ አጠራር መረጃ ምግቤ ነው የሚሉ ከሆነ፤ ያለ ምንም ጥርጥር ፌስ ቡክን የመሰለ ምርጫ የለም። ጨዋታ ቢልዎትስ ጨዋታ ብቻ ነው እንዴ…!? መንፈሳዊ ቢሉ፣ አለማዊ ቢፈልጉ፣ ፖለቲካዊ ቢሻዎ… በያይነቱ ጨዋታ የት ነው የሚገኘው? ምንም ጥርጥር የለውም ፌስ ቡክ ላይ ነው። ከቤተ መንግስት ጀምሮ እስከ ቤተ ግለሰብ ድረስ ያለው ቡጨቃ ቀላል ነው እንዴ…? የምሬን ነው የተተነፈሰችዋ ሳትቀር አንዲትም ጨዋታ አታመልጥዎትም…!
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ::
ሰሞኑን የአውሮፓ ዋንጫ በመሆኑ በተጨማሪም መጨው የለንደን ኦሎምፒክ በመሆኑ የፍሰሀ ተገኘን ብሎግ መጎብኝት ግድ ይሎታል:: በተለይ ደግም በአዲስ አበባ ኤፍሞች አታካች ስፖርታዊ “ትንተናዎች” የሰለቹ ከሆኑ የፍሰሀ ብሎግ ሁነኛ አማራጭ ነው:: ፍስሀ በዚህ ሳምንት በርካታ ጽሁፎች አቅርቧል:: ከነዚህ ውስጥ ስለ ቀነኒሳ የጻፈው ስቦኛል:: አንድ አንቀጽ፦
ታላቁ የረጅም ርቀት ሯጭ ቀነኒሳ በቀለ ኖርዌ ኦስሎ ከተማ ውስጥ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ርቀቱን 13፡00.54 ደቂቃ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ አምስተኛ ደረጃን አግኝቶ ካጠናቀቀ በኋላ የመወያያ ርእስ የሆነው “ኢትዮጵያዊው ድንቅ አትሌት ይታወቅበት የነበረው አስደናቂ የአጨራረስ ብቃት የት ሄደ?” የሚለው ነበር።
ቀነኒሳ የምወደው አትሌት ስለሆነ ስለሱ የተጻፍን ጽሁፍ እዚህ ለብሎግ ለክለሳዬ አዋልኩት እንጂ ሁሉም ጽሁፎቹ አንጀት አርስ ናቸው:: ይህንን ጽሁፍ ጨምሮ ሁሉንም ጽሁች ለማንበብ እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ::በነገራችን ላይ ከሚቀጠለው ሳምንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሎጎች ክለሳ ወደ ዞን ናይን ይዞራል:: መልካም ንባብ