የኢትዮጵያ ብሎጎች ምን ጻፉ?

የአሁኑን ሳምንት የኢትዮጵያ ብሎጎች ክለሳ ስሰራ ትልቁ ተግዳሮቴ የነበረው አብዛኞቹ ካሁን በፊት በዘዴ ወኪል ሰርቨርን በመጠቀም የማነባቸው ብሎጎች አብዛኞቹ ወኪል ሰርቨሮችም ጭምር ስለታገዱ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ድረስ ማንበብ አልቻልኩም ነበር:: ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ በወኪል ሰርቨሮች በኩል ማንበብ ያቃተኝን ጽሁፍ ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቼ እንዳለ ገልብጠው በውስጥ የኢሜል አድራሻዬ በኩል እንደ ቅጥያ ዶክመንት ልከውልኝ ማንበብ ችያለሁ:: ሌሎች ያልታገዱ አዳዲስ ወኪል ሰርቨሮችንም እንድሞክራቸው ልከውልኝ መጠቀም ችያለሁ:: ስላጋጠመኝ ችግር እና የሳምንቱ አብይ ጉዳይ ሆኖ የብዙ ብሎግ ጻሀፊያንን ትኩረት ስቦ ስለነበረው የብሎጎች እገዳ ይህችን ታህል ካልኩ ሌሎች ምን እንዳሉ እስቲ ላቃምሳችሁ:: በፍቄን ላስቀድም በፌስቡክ ግድግዳው ላይ አጭር ጽሁፍ አስነብቦ በብሎጉ ላይ ኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች በሚል ርእስ የጻፈውን ጽሁፍ ትይይዝ አስቀምጧል:: ሙሉውን ጽሁፍ ትይይዙን ጠቅ በማድረግ ይከፈቱት አልከፍት ካሎት በፍቄ በፌስቡክ ግድግዳው ላይ ያሰቀመጠውን ጽሁፍ በማንበብ ይሞክሩት:

“መንግስት ለምን ትንንሾቹን – ሰላማዊዎቹን ሰዎች ለማጥቃት በርካታ ገንዘብ እና ጊዜ እንደሚያባክን አልገባኝም:: ዛሬ የጻፍኩትን ጽሁፍ እኔ ራሴ ማንበብ እንዳልችል ሆኖ ታግዷል:: የሚገርመው በጽሁፉ ውስጥ ሐሳብን በነፃ ስለመግለጽ መብት የተናገርኩት ነገር ነበር:: በፕሮክሲ በመታገዝ ለመክፈት ስታገል ጉግል ራሱ .com የነበረውን .ca በማድረግ ያለፕሮክሲ እንድከፍተው ታድጎኛል:: ያው እናንተም ይህንኑ ተከተሉ:”

ብሎግ ማገድ ፈጽሞ የማይቻል ነገር እየሆነ መምጣቱን ቻይናውያንም ጠንቅቀው ያውቁታል:: ለነገሩ ቻይናውያን እንኳ ሲያግዱ አይናቸውን አፍጠጥው አላገድንም አይሉም ድድ ላይ የማይላከክ ምክኒያት እንኳ በትንሹም ቢሆን ይሰጣሉ እንጂ::
ወደ አቤ አለፍኩኝ በዚህ ሳምንት ከማሸሟጠጥ በተጨማሪም ብሎግ መክፈትም ስራዬ ሆኗል ብሎ በፌስቡክ ግድግዳው ላይ የጻፈው አቤ :ለ7ኛ ግዜ ብሎግ ከፍቷል:: አቤ ድብብቆሽ የሚጫወት እስኪመስል ድረስ በዚህ መጣሁ በዚህ ሾለኩ እያለ ብሎግ ሲከፍት እጁ የነካውን ሁሉ ማግድ በውነት ትዝብት ላይ የሚጥል ነው:: ይሄ ልጅ ምን ቢጽፍ ነው እንዲህ እጅ እጁን እየተከተሉ የሚዘጉት ለምትሉ ለ7ኛ ግዜ በከፈተው ብሎጉ የአንጋፋው ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄርን አንድ ጨዋታ ጨምሮ በርካታ በርካታ ጨዋታዎችን አስነባቧል:: ካልታገደ ትይይዙን ጠቅ በማድረግ ይሞክሩት:: መንግስት በእውነት የግለሰቦችን ብሎግ እየተከታተለ ይዘጋልን? እኔ ግን መንግስት እንዲህ ያለውን ነገር ይፈጽማል ብይ ማመን ይከብደኛል:: ይህ ጉዳይ ሰፊ እና ለብቻው ሰፊ ዘገባ የሚሻ ስለሆነ ወደ ብሎግ ምልከታዬ ልመለስ::

ቀጠልኩ እግር ኳስ የምትከታተሉ ሰዎች ያለፈውን ሳምንት የምታስታውሱበት በርካታ ነገሮች ተከስተው ነበር:: የባርሴሎና ከአውሮፓ ቻምዮኖስ ሊግ መወገድ ግን አንዱ እና ዋንኛው ነው:: ይህንን ጨዋታ ዳንኤል ክብረት የነብሴ ጨዋታ ይለዋል:: ለምን ይሆን የነብሴ ጨዋታ ያለው እስቲ አንድ አንቀጽ እንደ ማጓጓያ:

ከጨዋታው በፊት ባርሴሎና ቼልሲን በኑካምብ ሜዳ ላይ ድባቅ ሊመታው እንደሚችል የሚተነብዩነበሩ፡ ቼልሲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያለውን ቦታና ሰሞኑን ያስመዘገባቸውን ደካማ ውጤቶችተንተርሰውባርሴሎና ያሰለፋቸውን ምርጥ ተጨዋቾች ቆጥረው፣ የአሰልጣኝ ጋርዴዎላን ብቃትአሞካሽተው ለቼልሲ የፈሩለት ብዙዎች ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲበድሮግባ ጎል ባርሴሎናን አንድ ለባዶ ቢያሸንፍም፤ያ ግን አጋጣሚን እንጂ የቼልሲን ብቃት፣የባርሴሎናንም መውረድ እንደማያሳይ የተከራከሩ ነበሩ፡፡ «ደርሶ አይቼው» አለ አማራ ለልጁ ስም ሲያወጣ፡ ትናንት ደረሰና ሁሉንም አየነው፡፡ የተጠበቀውቀርቶ ያልተጠበቀው ሆነ እኔም ከጨዋታው በኋላ ነፍሴን እንዲህ አልኳት፡፡ ነፍሴ ሆይ በርቺ፡፡ ተስፋም አትቁረጭ ምናልባት ከፊትሽ የምትጋጠሚው ፈተና በዓለም ላይ ወደርየሌለውና ለማሸነፍ ከባድ መስሎ የሚታይ ይሆን ይሆናል፡፡ ምናልባትም ብዙዎቹን የረፈረፈ፤ ታላቅስምም ያተረፈ ይሆን ይሆናል፡ ምናልባትም ደግሞ የዓለም ሻምፒዮናነትን ክብር የተቀዳጀ ታላላቅየተባሉትን ሁሉ ድል እየመታ የመጣም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ነፍሴ ሆይ በርቺ፡

ዳንኤል ክብረት በሳምንቱ ይህንና ሌሎች ጽሁፎችንም አስነብቧል:: እዚህ ላይ ጠቅ በማድረግ ያንብቡት::

ስነጽሁፍ በተለይ ግጥም የምትወዱ ከሆናችሁ በዚህ ሳምንት ብሎጎች በርካታ ግጥሞች አስነብበውናል:: ተስፋዬ ገ/አብ መራር ስነግጥሞች በሚል ርእስ የበርካታ እውቅ ገጣሚያንን ግጥሞች አስነብቧል:: ከመንግስቱ ለማ ቀንጨብ ያደረገውን ላካፍላችሁ::

ባልን ቢያስተያዩት – ከሚስቲቱ ጋራ፣
እሷ አፍለኛ ሆነች – ያ! ሻጋታ እንጀራ፣

በሌሎቹ ስነግጥሞች ለመደሰት ትይይዙን ጠቅ ያድርጉት:: ታዲያ ካልከፈተ ከላይ የበፍቄን ምክር አይዘንጉ:: ለሌሎችም ብሎግ ስፖት (blogspot)ላይ የሚገኙ ብሎጎችን ለመክፈት ይጠቀሟቸው:: ከስነግጥም ብሎጎች ሳንወጣ አደም ሁሴን ናፍቆቴን ነጠቁኝ የሚል ግጥም አስነብቦናል:: እዚህ ላይ ጠቅ በማድረግ ዘና ይበሉበት::

በዚህ ሳምንት ተስፋዬ አለማየሁ ስለ ኢትዮጵያዊ መፈክሮች ስለታሪካዊ አመጣጣቸው እና ስለ ተጽእኗቸው አስነብቦናል:: እንደ ማጓጓያ አንድ አንቀጽ ላካፍላችሁ:: ቀሪውን እናንተ ትይይዙን ጠቅ በማድረግ ያንብቡት::

ህብረተሰባዊት ኢትዮጵያን መሰርተው አንድ ቋንቋ ተናግረው፣ አንድ ጥይት ተኩሰው፣ አንድ አቢዮት አፈንድተው፣ አንድ ትውልድ ፈጅተው፤ በጡጫ እና በግልምጫ ልቀው ከወጡት የወቅቱ መሪ ስም ጋር. . .ወደፊት፣ “ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር” እያሉ ይፎክሩ ነበር፡፡ በየመድረኩ በሚደረጉ ህዝባዊ ስበሰባዎችና ንግግሮች ላይም “እናት ሃገር ኢትዮጵያ ወይም ሞት” ፣”ህብረሰባዊነት ይለምልም”፣ “. . . ለኢምፔሪያሊስቶች “

አካባቢ የተባለ ብሎግ ስለ ጾም እና አካባቢ ትይይዝ መሳጭ በሆነ ቋንቋ አስነብቦናል:: እዚህ ላይ ጠቅ በማድረግ ግንዛቤዎትን ያዳብሩበት::

ክረምት ላይ ኢትዮጵያውያን በጉጉት የሚጠብቁት የለንደን ኦሎምፒክ ይካሄዳል:: በዳጉ የአለም አትሌቲክስ ሻምዮና ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ውጤት ደካማ ስለነበረ በለንደን ውጤታችን ምን ይሁን ብለው የሚጠይቁ ኢትዮጵያውያን ብዙ ናቸው:: ስለዚህ በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያን በለንደን ኦሎምፒክ እነማን ይወክሏታል? የሚለውን የፍሰሀ ተገኝን ጽሁፍ ማንበብ ደግሞ በዳጉ የአለም አትሌቲክስ ሻምዮና የተመዘገበው ደካማ ውጤት እንዳይደገም በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክሉትን አትሌቶች በጥንቃቄ እና በርካታ መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ ያስገባ መረጣ እንዲደረግ ያስገነዝባል:: አንድ አንቀጽ እንካችሁ:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በምርጫው ላይ ከአመታዊ ፈጣን ሰአቶች በተጨማሪ እንደ ጸጋዬ ከበደ ያሉ በታላላቅ የአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የአሸናፊነት ልምድ ያላቸው አትሌቶችን ለለንደኑ ኦሎምፒክ ማካተት አለበት። በአለፈው እሁድ ለንደን ላይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ሶስተኛ የወጣው ጸጋዬ፤ በ2009 ዓ.ም የለንደን ማራቶን አሸናፊ፣ በቤጂንግ ኦሎምፒክ የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤትና በበርሊኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት ነው። የጸጋዬ ከበደ ጠንካራ ጎን ብቃቱ የማይዋዥቅ መሆኑና በአብዛኛው ፈጣን የሚባሉ ሰአቶቹን ያስመዘገበው አስቸጋሪና ፈታኝ እንደሆኑ በሚነገርላቸው ለንደን፣ ኒው ዮርክ እና ቺካጎ ከተሞች ውስጥ በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ላይ ነው። የሚገርመው በእነዚህ አስቸጋሪ የማራቶን መወዳደሪያ ስፍራዎች ቢሮጥም ያስመዘገባቸው ሰአቶች በአማካይ 2 ሰአት ከ06 ደቂቃዎች መሆናቸው ነው።

ፍስሀ ሌላም ማራኪ ጽሁፍ አስነብቦናል ስለ ባርሴሎናው ድንቅ ልጅ ፔፕ ጋርድዮላ:: ፔፕ ከባርሴሎና አሰልጣኝነት አራት ድንቅ የውድድር አመቶች ካሳለፈ በኋላ እንደማይቀጥል ይፋ በማድረጉ በርካታ የአለም መገናኛ ብዙሀን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል::ስለዚህ ድንቅ እና ትሁት ካታሎናዊ ለኢትዮጵያውን በሚመች የአተራረክ ዘይቤ ቀርቧል:: እዚህ ላይ ጠቅ በማድረግ ይዝናኑበት::

3 thoughts on “የኢትዮጵያ ብሎጎች ምን ጻፉ?

  1. I would say internet censorship is in high pick right now. Following the incidents after 2005 elections, in which a lot of people died with bullets fired by army forces, this time around shows high level blockage on the social media. I am wondering why the traditional media, newsletters and FM radios don’t talk about this???????? aren’t they almost 100% relay on the information on the internet now a days? and aren’t they copy-paste what people in citizen media reflects in the internet? at least, they should fight for the source of information – if not for freedom of speech! I really encourage many people start writing and sharing instead of just reading – this will definitely create a lot of pressure for whoever is behind the website blocking.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.