የኢትዮጵያ ብሎጎች ምን ጻፉ?

በዚህ ሳምንት በእንሊዝኛም ሆነ በአማርኛ ብዛ ያሉ አንጅት አርስ የሆኑ ጽሆፎች፡ትንተናዎች እና ቃለመጠይቆች በኢትዮጵያ ብሎጎች (ጦማሮች) ተነበዋል። የእንሊዝኛውን ወደ በኋላ እመጣበታለሁ አሁን ቀልቤን ውደ ሳቡት የዚህ ሳምንት የጦማር ጽሆፎች ልለፍ። በነገራችን ላይ ብሎግ የሚለውን የእንግሊዘኛ ቃል ጦማር ብሎ ማን ወደ አማርኛ እንደተረጎመው ባላውቅም ቃሏ ግን ተመችታኛለች በመሆኑም ከዚህ በኋላ በቋሚነት ጦማር የምትለዋን ቃል ብሎግ በምትለዋ እንድትተካ ተወዳጅ የአማርኛ ጦማሬያንም ቢጠቀሙባት:: ካልኩ በኋላ ወደ ክለሳዪ ልፍጠን::

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ጦማሮች ምን ጻፉ? በሚል ርእስ በጻፍኩት ክለሳ ኣንድ የፌስቡክ ወዳጄ እንዲህ ብሎኝ ነበር::
“እንግዲህ እየቃረምክ በ”አጤሬራ” መልክ አምጣልን:: አደራህን አቤ ቶክቻውን እንዳትረሳብኝ:: ልክ ምርጥ ሽሮ ወጥ ሲሰራ መከለሻ ይጨመራል አይደል? የአቤ ቶክቻውም እንደዚያው ነው:: ምርጥ መከለሻ ሆኖ ጽሑፍህን ያጣፍጥልሃል: አቤ ቶክቻው በአሸባሪነት ከተመዘገበ ግን ወንድሜ አንብበው እንጅ እንደ መረጃ ተጠቅመህ አትጻፈው::” ምክሩን ተቀብያልሁ።አቤ ቶክቻው በአሸባሪነት ስላልተፈረጀ ግን ከአቤ ልጀምር፦

በነገራችን ላይ አቤ በዚህ ሳምንት አልተቻለም። ያውም በሁለት ጦማር እኮ ነው። ለሀገር ውስጥ እና ለዳያሰፖራ አንባቢዎች፡ እንደ አይጥ በሁለት ጉድጓድ እየተጫወተ ነው። እሁድ ለት “ታላቁን” የህዳሴ ግድብ ምስራታ ምክንያት በማድረግ “ዕርቲስቶች”ዕርቲስቶች እና ፖለቲከኞች የእግር ኳስ ውድድር ኣካሂደው ነበር:: ይህንን በማስደገፍ አቤ እግር ኳስን በብሎግ ይመልከቱ በሚል ርእስ ያስነበበው ጽሁፍ በዛ ቁም ነገሮች በውስጡ ኣምቆ ይዟል:: ኣባይ የሚባለውን ተጫዋች ህዝቡ ቢውደውም ኣሰልጣኙ ወደ ጨዋታው ያስገቡት ዘግየት በለው ስለሆነ ተጫዋቹ ትንሽ የመደናገር ባህሪይ ይታይበታል ይለናል አቤ፦

ተመልካቾቻችን አሁን ኳስ ለአባይ ደርሳለች። አባይ ኳሷ ድንገት ስለደረሰችው የተደናገጠ ይመስላል። ኳስ ከያዘ በኋላ ሜዳው ላይ ባልተለመደ መልኩ ሚሊኒየም የሚል መለያውን ቀይሮ ህዳሴ የሚል ሌላ መለያ ለብሷል። በእውነቱ ይሄ የሚያስቅ ነው። ኳስ አመታቱም ግራ የሚያጋባ ነው አንድ ግዜ አምስት ሺህ ሌላ ግዜ ደግሞ ስድስት ሺህ ይለጋል። ኦያያያ… አባይ ምንም አልተዘጋጀም። ኢህአዴግ አሁን አባይን እንደ ራሱ ተጫዋች እየቆጠረው ነው። አታለል… ኢህአዴግ አታለል!!! ህዝቡም በአባይ አጨዋወት ግራ ቢጋባም ተወዳጅ ተጫዋች በመሆኑ እየዘመረለት ይገኛል። ኦ ያያያ… የኢህአዴግ አጨዋወት ግራ ነው የሚያጋባው። ተመልካቾቻችን ጨዋታው እንደቀጠለ ነው። የኑሮ ውድነቱ ኳሷን እንደያዘ ነው። በመከላከል ረገድ የህዝቡ አለኝታ የሆኑ ሃይማኖቶች አሁንም ከኢሃዴግ አጥቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል። ከህዝቡ ወገን የነበሩ አንዳንድ “ሀብቴ የህዝብ ፍቅር ነው” ሲሉ የነበሩ አርቲስቶች ከኢህአዴግ ጎን ተሰልፈዋል።
አቤ ይህንን እና ሌሎች በርካታ ጽሆፎችን በሁለቱ ጦማሮች ኣስኮምኩሞናል:: እዚህ ጋር ተጨነው ፍታ በሉባቸው::

ስደት በየፈርጁ፥ በአካል፣ በቅዠት፣ በሆድ፣ በመንፈስ ፣ በትዕቢት በሚል የስደት እና የኢትዮጵያውያንን ኣስከፊ ግንኙነት ኣቤል ምሁራዊ ኣስተያዩትን ዘርዘር ባለ ጸሁፉ ኣስቃኝቶናል። የራሶዎትን ኣስተያዩት ከዚህ ጻሃፊ ኣንጻር ለመለካት ከፈለጉ ይህችን ትይይዝ ጠቅ ያድርጓት::

ተስፋዬ ገብረአብ ብሎጉ ኢትዮጵያ ውስጥ መከፈት ኣለመከፈቱን የፌስቡክ ወዳጆቹ ኣንዲያጣሩልት በፌስቡክ የጠየቀው በዚህ ሳምንት ወደ ጎንደር የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ለማስተማር የመጣ አንድ ጀርመናዊ ሃኪም አንዲት የገበሬ ሚስት እያከመ ከባልየው ጋር እሰጣ ገባ የገጠሙበትንጉዳይ የበጌምድር ገበሬ የክብር ጉዳይ ከኛ ዘመን ትውልድ ጋር የመንፈስ ዝምድና ይኖረዋል ለማለት ቃጥቶኝ አያውቅም። ይላል ተስፋዬ ሙሉውን ጽሁፍ ለማግኘት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ:: በነገራችን ላይ ስለ ብሎግ መከፍት ስናወራ ባለፈው ሳምንት ታግድው የነበሩት ብሎጎች መለቀቃቸውን በማስመልከት ኣቤም ኣንድ ብሏል:: በነካ እጃቻው ሌሎችንም የታግዱ ድረገጾች ቢለቁልን። ይህን የምለው ግን ለራሳቸው ብየ ነው:: እኔማ በጓሮም ቢሆን እየገባሁ
ኣነባቸዋለሁ::
ሌላው በዚህ ሳምንት ከተነበቡ ብሎጎች ከፍተኛ ተደማጭነት እያገኝ የመጣውን የድምጻዊ ጃሉድን ቃለመጠይቅ ያቀረበው ሽገር ትሪቡን የሚባለው ብሎግ ነው:: የድምጻዊውን የህይወት ውጣ ውረድ በሚገባ ያስቃኞታል:: ኣንብቡት::

እንዲህ እንደዛሬው በርካታ የስፖርት ጋዜጠኞች ሳይበራከቱ በኤፍኤም አዲስ ብዙ የአዲስ አበባ ኗሪዎች ጣፍጭ ስፖርታዊ ወሬዎችን እጅግ በተደራጀ ሁኔታ ሲያቀርብ ፍሳሀ ተገኝን ብዙዎች የምታስታውሱት የናፈቃችሁም ይመስለኛል:: ግን ደግሞ አይዞን ፊሽ በሚጣፍት ቋንቋ ለዛ ያላው ያኣትሌቲክስ፡ የእግር ኳስ ፡ እና የሌሎችንም ስፖርቶች ዘገቦች በብሎጉ ያቅርብላቹኋል:: በዚህ ሳምንት ጃፓናውያን ሴቶች በፍቅር ስላበዱለት የማራቶን ጀግና አበበ ቢቂላ ያሰነብባቹኋል:: ለነገሩ ይነግራቹኋል ብል ይቀለኛል:: ስታነቡት የሚያንብላችሁ ያህል ነው የሚሰማችሁ:: ከመግቢያው፦

በአንድ ወቅት ጃፓናውያን ሴቶች አብረውት ለመሆን በቁጥር አንድነት የሚመኙት ጎረምሳ ነበር። እሱ ያለበትን ሁኔታ በንቃት ይከታተላሉ፣ ባዩት ቁጥር በደስታ ይጮሀሉ። ስለ ብራድ ፒት ወይም ዴቪድ ቤካም እያወራሁ አይደለም፤ ስለ አበበ ቢቂላ እንጂ። እ.አ.አ በ1961 ዓ.ም በጃፓኗ ኦሳካ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ ተሳትፎ በአሸናፊነት ካጠናቀቀ በኋላ በጃፓናውያን ሴቶች ልብ ውስጥ መግባት የጀመረው አበበ ቢቂላ በ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ወደጃፓን ሲሄድ በሰውነት አቋማቸው ከሚበልጡትና በእድሜ ከሱ ከሚያንሱት ፈርጣማና ጡንቸኛ አሜሪካዊን የኦሎምፒኩ ተሳታፊዎች ቦክሰኛው ጆን ፍሬዠርና ዋናተኛው ዶናልድ አርቱር ሾላንደር ይልቅ የሀገሪቷን ሴቶች ቀልብና ልብ መስረቅ ችሏል።

ቀሪውን ለራሳችሁ እዚህ ይጫኑ:: ሳምንት ሌሎች የኣማርኛ ብሎጎችን ይዤ እቀርባሁ:: ለእንሊዝኛ ቋንቋ አንባቢዎቼ ነገ የእንሊዝኛ ብሎጎች ክለሳዪን ይጠብቁ:: መልካም በአል::

3 thoughts on “የኢትዮጵያ ብሎጎች ምን ጻፉ?

  1. ኮይ፥ ሁሌ እንዲ oh man, i am having problems with writing in amharic.. i couldn’t find all the words… where are the tech people now? we should fix the amharic keyboard problems… enough on this, but thanks again for summarizing the blogs. keep update us!

Leave a reply to Meron Mamo Cancel reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.