ታላቁን የሚሊንየም ግድብ በተመለከተ ከተሰሙ ሰሞነኛ ንግግሮች

አንድ ወዳጂ ሰሞኑን በአባይ ወንዝ ላይ ሊሰራ የታቀደው የታላቁ የሚሊንየም ግድብን በተመለከተ ከሚካሂዱት የውይይት መድረኮች አንዱ ላይ ተግኝኝቶ አንድ ተናጋሪ ሲናገር ሰማሁ ብሎ ያጫወተኝ ፈገግ ያሰኛል ፡፡ ንግግሩ ቅልብጭ ከማለቱ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሰ ነው፡፡

የስብስባው መሪ እድሉን ለተናጋሪው ሲሰጡት አስተያየቱን እንዲያሳጥር አሳስበውት ነበር፡፡ ተናጋሪውም ትዕዛዝ አክባሪ ነበርና፡፡ አስተያየቱን እንዲህ ጀመረ፡ ˝ ለዘመናት አያት ቅድም አያቶቻችንን ሲያስቆጭ የነበረው አባይ በእኛ ዘመን ለዚህ አይነት ወግ ማዕረግ መብቃቱ በውነት የሚያረካ ተግባር ነው፡፡ በተለይ መንግስታችን በእድገት እና ትራንስፎርሚሽን ዘመን ይህን ማስቡ ሊያስመሰግነው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ግብጽ በእሁኑ ሰአት በከፍተኛ የህዝብ አመፅ እየታመስች ሰለሆነ የታላቁን የሚሊንየም ግድብ ፕሮጀክት በሰላም ማስፈፅም እንችላለን፡፡ አንድ አንድ ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያ ውስጥም የግብጽ አይነት ህዝባዊ አመፅ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ይናገራሉ ነገር ግን ይህ የግብፅን ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥነት ችግር እና የዋጋ ግሽበትን መሰረት ያረገ ህዝባዊ አመፅ ካለመረዳት የሚመነ ጭ ነው ፡፡ምክንያቱም በኢትዮጵያ ዜጎች የስራ አድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ከዚህም በላይ መንግስት ለሰራቶኞች ከፍተኛ የሆነ የደሞዝ ጭማሪ አድርጓል ፡፡ መንግስት ይህንን የሚያደርገው በቅርቡ የተክሰተውን የዋጋ አለመረጋጋት ለማስከን ዕንደሆነ ይታወቃል ቢሆንም የገበያውን ሁኔታ ወደ አልተረጋጋ ሁናቴ ለማድረስ የሚፈልጉ አንድ አንድ ስግብግብ ነጋዴዎች የሉም ማለት አይደለም ይህ ማለት ግን ሁሉም ነጋዴዎች በአቋራጭ ለመክብር የሚፍ,ፈልጉ ጥማታሞች ናቸው ማለት አይደለም ፡፡ ነግር ግን አንድ አንድ ገለሰቦች የነጋዴዎን ማህበረስብ በአንድ ለመፈረጅ ይሞክራሉ፡፡ በተለይ የነጋዴው ማህበረሰብ በብዛት የአስልምና ሀይማኖት ተከታ ከመሆኑ አንፃር ሙሰሊሙን መህበረስበሰ በአንድ መፈረጅ የኢትዮጵያን ታሪክ በቅጡ በለመገንዘብ የሚመጣ የጥገኝነት አባዜ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ምክኒያቱም ሙሰሊሙ በኢትዮጵያ ታሪክ ከንጉስ አል ነጃሺ ጀምሮ ለሀገራችን ኢኮነሚያዊ ;ማህባራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ ከፍተኛ አስተመወፅኦ ያበረከተ ማህበረስብ ነው፡፡”

አስተየያቱን ለመቀጠል ትንፋሹን እያሰባሰበ ሳለ በኪሱ የያዛት የቻይና ሞባይል ዙምባራ ዙምባራ በሚል ዘፈን የስልክ ጥሪ ከባድ ⶼህት ተሰብሳቢውን ግማሹን ከደሞወዝ ለግድቡ ማሰሪያ ስንት ፐርሰንት ይቆረጥ ይሉ ይሁን ከሚለው ጭንቀትና የርስበርስ ወሬ ግማሹን ካንቀላፋበት ቀሰቀሰው፡፡ በዚህ ማህል ሰብሳቢው ተናጋሪው አስተየያቱን አንዲቋጭ ሲያሳስቡት አስተየያቱን በጥያቄ እንዲህ ሲል ቋጨ፡ ˝ አሁን ግድብን ማሰሪያ ለሚሆን የምንገዛው ቢድ ቦንድም ሆን ቦንድ በፍላጎት ወይስ በግዳጅ ነው የምንገዛው ?˝ ብሎ አጥረ ያለ ጥያቄያዊ አስተየያቱን ሲያበቃ ተሰብሳቢው ሞቅ ባለ ጭብጨባ አጀበው፡፡

2 thoughts on “ታላቁን የሚሊንየም ግድብ በተመለከተ ከተሰሙ ሰሞነኛ ንግግሮች

  1. I canread the article Endlk
    ሙሰሊሙን መህበረስበሰ በአንድ መፈረጅ የኢትዮጵያን ታሪክ በቅጡ በለመገንዘብ የሚመጣ የጥገኝነት አባዜ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ምክኒያቱም ሙሰሊሙ በኢትዮጵያ ታሪክ ከንጉስ this was the format in my PC

  2. ሰውዬው ክቦ ክቦ ( ታሪካዊ ክስተት መሆኑን ገልጾ) መጨረሻ ላይ ቦንዱን በግድ ነው በፍላጎት ማለቱ አልተዋጠልኝም፡ የህ የሚወራው ነገር እውነት ከሆነ የዜግነት ግዲታ ስላለብን የተወሰነ ማዋጣቱ አይከፋም ! ግን ነገሩ ተዘሎ የሚገባበት መሆን የለበትም! ብዙ ቅድመ ሁኒታዎች የሚያስፈልጉት ስለሆነ መንግሰት ምን ያህል እንዳሰበበት ፍርሃት አለኝ!! በደንብ አስቦበት “ ሰፕራየዝ” ለማለት ፈልጎ ይሁን ወይም ለጫወታ “ አፕሪል ዘ ፉል” . . . !

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.